ኢንቪዲያ ኩባንያ ኦፕን ኤ.አይ ላይ የ100 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ዕቅድ ይፋ አደረገ፡፡
· Computer Vision
የአሜሪካው የቴክኖሎጂ ኩባንያ የሆነው ኢንቪዲያ በኦፕን ኤ.አይ ላይ 100 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት እንደሚያደርግ አስታውቋል።
የኢንቪዲያ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጄንሰን ሁዋንግ የኢንቨስትመንት ዕቅዱ የሚቀጥለውን የእውቀት ዘመን የሚያንቀሳቅስ እንደሆነ ተናግረዋል።
ኢንቨስትመንቱ ለኦፕን ኤ.አይ ለቀጣዩ ትውልድ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት የሚያገለግል የዳታ ማዕከላት ግንባታ እንደሚውል ተነግሯል።
ኢንቪዲያ ይህንን ከኦፕን ኤ.አይ ጋር የሚደረግ ጥምረት "ስትራቴጂያዊ ሽርክና" በማለት ገልፆታል። በመሆኑም ድርጊቱን በዓለም አቀፉ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ፉክክር ውስጥ ያሉ የሁለት ታዋቂ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የቅርብ ጊዜ ትልቁ እርምጃ ብሎ ቢ.ቢ.ሲ በድረ ገፁ አስነብቧል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute