ኤአይ ዓለምን እየቀየረ ነው፤ ለኢትዮጵያ ምን ማለት ነው?
· AI Solutions
Stanford HAI’s 2026 Report Highlights Rapid AI Progress, Intensifying US–China Competition, and the Urgent Need for Responsible Governance
የስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ሰዎችን ማዕከል ያደረገው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ተቋም (Stanford HAI) የ2026 አዲስ ሪፖርት ይፋ ሆኗል።
ሪፖርቱ የሰው ሰራሽ አስተውሎት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከቀን ወደ ቀን በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ መምጣቱን እና አሁን በዶክትሬት (PhD) ደረጃ ያሉ ጥያቄዎችን እና የሂሳብ ውድድሮችን እስከ መመለስ የሚችልበት አቅም ላይ እንደደረሰ አሳይቷል።
በአሜሪካ እና በቻይና መካከል ያለው የቴክኖሎጂ ብቃት ውድድር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠበበ መጥቷል፡፡ አሜሪካ ዘመኑን በዋጁ የዳታ ማዕከላት እና በግል ኢንቨስትመንት ስትቀደም ቻይና ደግሞ በምርምር ሥራዎች እና በፈጠራ ብዛት ግንባር ቀደም ሆናለች።
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ እድገት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ቢመጣም ኃላፊነት የሚሰማው አጠቃቀም እና የደህንነት ቁጥጥር ግን በበቂ ፍጥነት
እያደገ እንዳልሆነ ተመላክቷል።
ይህ ሰፊ የዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ጉዞ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት የዲጂታል ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ አግባብነት ያለው ፖሊሲ ቀድሞ ማዘጋጀታቸው ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ አበክሮ ያሳያል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute