የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የኤ.አይ ክበብ መሠረተ።
· Education
EAII Expands School AI Clubs in Dire Dawa to Build Future-Ready Digital Talent.
የኢንስቲትዩቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ዘውዴ በምሥረታ መርኃ ግብሩ ላይ ንግግር አድርገዋል። ኤ.አይ ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው የገለፁት ዳይሬክተሩ፤ ኢንስቲትዩቱ ታዳጊዎችን ለማብቃት በተለያዩ ትምህርት ቤቶች መሰል ክበባት ሲያቋቁም መቆየቱን አንስተዋል። ይህም ኢንስቲትዩቱ በዘርፉ ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት እንደ ሀገር እየሰራቸው ከሚገኙ ስራዎች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በድሬዳዋ ትምህርት ቢሮ የክበባት አስተባባሪ አቶ አስቻለው ሸዋረጋ በበኩላቸው ተማሪዎች ዕድሉን እንዲጠቀሙበት አሳስበዋል። አክለውም ለክበቡ ውጤታማነት ቢሯቸው ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል።
የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ክንዴ ቶሎሳ ተማሪዎቹ በዘርፉ ያላቸውን አቅም ለማዳበር የክበቡ መቋቋም አጋዥ ነው ብለዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute