ለአንድ ወር ሲካሄድ የቆየው የኤ.አይ ክሬቲቭ አዋርድ የሙዚቃ ውድድር ተጠናቀቀ
· Education
EAII AI Music Competition Concludes, Showcasing Creative Innovation, Cultural Heritage, and Digital Economic Growth
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እና ከእሁድ ኤ.አይ ስቱዲዮ ጋር በመተባበር የኤ.አይ የሙዚቃ ውድድር ሲያካሄድ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
600 ሙዚቃዎች ለውድድር ቀርበው በዳኞች እና በህዝብ ድምፅ አሸናፊዎች ተለይተዋል፡፡
ውድድሩን አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ለፈጠራ እና ለበጎ ዓላማ ለማዋል ኢንስቲትዩቱ ከተቋማቱ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፈጠራ ውድድር ቴክኖሎጂው በጥበብ ዘርፍ ያለውን አቅም ከማሳየት ባለፈ
የሀገራችንን አኩሪ ታሪክ በቴክኖሎጂ እና የጥበብ ጥምረት መግለፅ ያስቻለ ነው ብለዋለ፡፡
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ በበኩላቸው ይህ አይነቱ ውድድር ቴክኖሎጂን ለመጠቀም እና ከዘመኑ ጋር አብሮ ለማራመድ እንዲቻል አዲስ መንገድ የከፈተ በመሆኑ ሊደነቅ እንደሚገባው ጠቁመዋል፡፡
የሀገራችንን የጀግንነት ታሪክ በጥበብ ለመዘከር ከቴክኖሎጂ ጋር በማዋሃድ የተካሄደው ውድድር፤ ቴክኖሎጂው ለፈጠራ ያለውን አቅም ከማሳየትም በተጨማሪ የኢትዮጵያን የቀደመ ታሪክ የአሁኑ ትውልድ እንዲረዳው በማድረግ ረገድ ውድድሩ ቁልፍ ሚና አለው ያሉት የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አድማሱ ዳምጠው ናቸው፡፡
በውድድሩ አንደኛ ለወጣው ኤፍሬም አሸናፊ የ5 መቶ ሺህ ብር፣ ሁለተኛ ለወጣው ኪሩቤል ታቡ 3 መቶ ሺህ እና በሶስተኝነት ላጠናቀቀችው ኬቲም ተስፋዬ የ2 መቶ ሺህ ብር ሽልማት ከዕለቱ እንግዶች ተበርክቶላቸዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute