የየኔታ አካዳሚ ተማሪዎች በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ትምህርታዊ ጉብኝት አደረጉ።
· Visiting
Grade 12 students from Yeneta Academy visited the Ethiopian Artificial Intelligence Institute to explore AI innovations and gain inspiration for future careers in technology.
ከየኔታ አካዳሚ የተዉጣጡ የ12ተኛ ክፍል ተማሪዎች በኢንስቲትዩቱ በመገኝት የኤ.አይ ቴክኖሎጂ አሁናዊ ዓለማቀፍ ገጽታ እና በሀገራችን ያለበትን የትግበራ ሁኔታ የሚያስገነዝብ ትምህርታዊ ምልከታ አድርገዋል።
በጉብኝቱ ኢንስቲትዩቱ ያለዉን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ የሚያስቃኝ ገለጻ ቀርቧል።
ተማሪዎቹ በኢንስቲትዩቱ የተመለከቱት ነገር እንዳስደሰታቸዉ ብሎም አዳዲስ ነገሮችን እንዳዩበት ተናግረዋል። በተጨማሪም በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ላይ እየተሰራ ያለዉ ስራ ወደፊት ዘርፉን ለመቀላቀል መነሳሳት የሚፈጥር ሆኖ ማግኘታቸዉን ገልጸዋል።
የየኔታ አካዳሚ ተማሪዎች በኢንስቲትዩቱ በነበራቸዉ ጉብኝት የሮቦቲክስ ወርክሾፕ፣ የምርት ማሳያ ክፍል፣ ዲጂታል ቤተ መጽሐፍት እንዲሁም የኤ.አይ
ስታርታፕ ማዕከልን ተዘዋዉረዉ ተመልክተዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute