ግዙፉ የቻይናው የኤአይ ኩባንያ አይፍላይቴክ ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ ለመስራት ተወያየ::
· Visiting
Senior executives from China’s iFlytek visited the Ethiopian Artificial Intelligence Institute to discuss cooperation in AI technology, local-language models, technology transfer, and support for Ethiopia’s upcoming AI university.
በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም የሆነው የቻይናው አይፍላይቴክ (iFlytek) ኩባንያ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በመገኘት በጋራ መስራት በሚችሉባቸው የቴክኖሎጂ ዘርፎች ዙሪያ ተወያዩ።
የልዑካን ቡድኑ አባላት በኢትዮጵያ ባዩት የቴክኖሎጂ ዝግጁነት መደነቃቸውን ገልጸው የኤ.አይ መተግበሪያዎችን ከኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ መረጃዎች ጋር በማጣመር ሀገሪቱን በአፍሪካ የቴክኖሎጂ ማዕከል ለማድረግ በትብብር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
የኢንስቲትዩቱ የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ እና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች አማካሪ ሻምበል ይልማ (ዶ/ር) በኢንስቲትዩቱ የበለፀገውን "መላ" የተሰኘ የቋንቋ ሞዴል እና የሀገር ውስጥ ቋንቋዎችን የማሽን ቋንቋ ለማድረግ የተከናወኑ ስራዎችን በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ሰጠዋል። የጽ/ቤት ኃላፊው አክለውም ኢትዮጵያ በአፍሪካ የመጀመሪያውን የኤአይ ዩኒቨርሲቲ በማቋቋም ላይ እንደምትገኝ እና ይህንንም የሚደግፍ ዘመኑን የዋጀ የዳታ ማዕከል መሰረተ ልማት መገንባቱን ገልጸው ከኩባንያው ጋር በትብብር ለመስራት ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።
ሁለቱ ተቋማት በኢትዮጵያ በሚቋቋመው የኤ.አይ ዩኒቨርሲቲ የእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ፣ የሀገር ውስጥ ቋንቋዎችን መሰረት ያደረጉ የቋንቋ ሞዴሎችንና የኤአይ መተግበሪያዎችን በጋራ ለማልማት፣ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች የኤ.አይ ቴክኖሎጂዎችን ለማላመድ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ተወያይተዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute