ሕንድ እ.ኤ.አ. በ2028 የ200 ቢሊዮን ዶላር የኤ.አይ መሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ለመሳብ አቅዳለች፡፡
· AI Investment
India unveils $200 billion plan to build AI infrastructure and position itself as a global technology hub by 2028.
ሕንድ እ.ኤ.አ. በ2028 ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረተ ልማት ከ200 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ ዕቅድ እንዳላት አስታውቃለች። ውጥኑ የዳታ ማዕከላትን፣ የኮምፒዩቲንግ አቅም እናየደጋፊ ቴክኖሎጂዎችን ሥነ ምህዳር በመገንባት ሀገሪቱን ዓለምአቀፍ የአ.ኤይ ማዕከል ለማድረግ ያለመ ነው።
እንደ ቴክ-ክረንች ዘገባ ይህ ግዙፍ የኢንቨስትመንተ ዕቅድ ሕንድን በዓለም አቀፍ የኤ.አይ ውድድር ውስጥ ብቁ ተወዳዳሪ ለማድረግ የተነደፈ ነው፡፡ ይህም የአገር ውስጥ እናዓለማቀፍ ኢንቨስተሮችን ለመሳብ ያለመ ነው፡፡
የዕቅዱ አብይ ስልት የሚያተኩረው በመጪዎቹ አመታት በተለያዩ ዘርፎች ፈጠራን እናኢኮኖሚያዊ እድገትን ያመጣል ተብሎ የሚጠበቁትን የኤ.አይ ምርቶች በማላመድ ሂደት ውስጥ የጀርባ አጥንት የሆነውን አካላዊ እናዲጂታል መሰረተ ልማትን በመገንባት ላይ ነው፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute