የሰደድ እሳት መነሻን በቅጽበት የሚለይ አዲስ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ተበሰረ
· AI Solutions
GenFire AI Technology Pinpoints Wildfire Origins and Tracks Early Spread with Greater Speed, Safety, and Accuracy
በደቡብ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች እና በካሊፎርኒያ የደንና የእሳት አደጋ መከላከል ክፍል ትብብት የለማው ቴክኖሎጂ ሰደድ እሳት የት እንደተነሳ በትክክል ለመለየት እና በመጀመሪያዎቹ 24 ሰዓታት ውስጥ እንዴት እንደተስፋፉ ለማጥናት የሚያስችል የመጀመሪያው መሳሪያ እንደሚሆን ተገልጿል።
አሁን ላይ ያሉ የሰደድ እሳት አደጋ ምርመራዎች በአካል በመገኘት እና በጥርጣሬ ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው ወራት ወይም ዓመታት ሊወስዱ ይችላሉ። ይህ የኤአይ ቴክኖሎጂ ሂደቱን ፈጣን፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ሳይንሳዊ ያደርገዋል።
ቀደም ሲል የነበሩ ዘዴዎች ከትክክለኛው መነሻ ቦታ እስከ 2 ኪሎ ሜትር ርቀት ድረስ ስህተት ሊኖራቸው የሚችል ሲሆን ጄንፋየር ግን ይህንን ስህተት ወደ 200 ሜትር ወይም 10 እጥፍ ያህል በመቀነስ እሳቱ የተነሳበትን ትክክለኛ ነጥብ ለመለየት ያስችላል።
በቅርቡ ስራውን በይፋ የሚጀምረው ይህ ቴክኖሎጂ በተፈጥሮ፣ በአደጋ ወይንም በሰው ሰራሽ ምክንያቶች የሚከሰቱ የእሳት አደጋዎችን በመለየት ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እና የምርመራ ሂደቱንም ለማቀላጠፍ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute