የኤ.አይ ቴክኖሎጂ የሶፍትዌር አልሚዎችን ስራ ውጤታማ እያደረገ መሆኑን ጥናት አመላከተ፡
· Machine Learning
በጉግል ክላውድ የሚመራው ዶራ (DORA) የተሰኘው የምርምር ፕሮግራም ባወጣው የጥናት ውጤት የሶፍትዌር አልሚዎች የኤ.አይ ቴክኖሎጂን በስፋት እየተጠቀሙት እንደሆነ አመላክቷል፡፡ ከመላው ዓለም የተውጣጡ 5,000 የሶፍትዌር አልሚዎች በጥናቱ ተሳተፈዋል፡፡
የጥናት ውጤቱ በሶፍትዌር ልማት ውስጥ የኤ.አይ ተካታችነት 90 በመቶ መድረሱን እና ብዙዎቹም በየቀኑ ለሁለት ሰዓት እንደሚጠቀሙበት ይገልጻል፡፡ በዚህም ከ80 በመቶ በላይ ምላሽ ሰጪዎች ኤ.አይ የስራ ውጤታማነትን እንደጨመረ የገለጹ ሲሆን 59 በመቶዎቹ ደግሞ ኤ.አይ የኮድ አጻጻፍ ጥራትን አሻሽሏል ብለዋል፡፡
ጥናቱ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሰውን የውሳኔ ሰጪነት ሚና ከመተካት ይልቅ ብዙዎች እንደ ደጋፊ መሣሪያ እየተጠቀሙበት እንደሆነ ያመላከተ ነው፡፡
ጉግል ክላውድ በድረገጹ ባወጣው መረጃ መሰረት ኤ.አይ በዘርፉ በተሰማሩ ተቋማት ውስጥ ያለው ተጽዕኖም በዚህ የ2025 የጥናት ውጤት ውስጥ ተካቷል፡፡
ዶራ በጉግል ክላውድ የሚመራ እና በዓለም ዙሪያ የሶፍትዌር ልማት አፈጻጸምን የሚዳስስ ዓመታዊ ሪፖርት የሚያቀርብ የጥናት ፕሮግራም ነው፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute