ኤአይ ለሁሉም፤ ጌትስ ፋውንዴሽን ለ ኤአይ ልማት አንድ ቢሊዮን ዶላር ሊያውል ነው።
· AI Investment
Gates Foundation Commits $1 Billion to Expand Equitable AI Access in Education, Health, Agriculture, and Digital Infrastructure
የጌትስ ፋውንዴሽን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂና መፍትሄዎች በዓለም ዙሪያ ተደራሽ እንዲሆኑ በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት አንድ ቢሊዮን የአሜሪካ
ዶላር ሊያውል መሆኑን አስታውቋል። ፋውንዴሽኑ የ2026 ዓመታዊ Goalkeepers Reportን በማስተዋወቅ ላይ ሲሆን የኤአይ ቴክኖሎጂ ለሁሉም
በፍትሃዊነት ተደራሽ እንዲሆን የዛሬ ውሳኔዎችና ኢንቨስትመንቶች ወሳኝ መሆናቸውን ገልጿል።
ፋውንዴሽኑ ሦስት ዋና ነጥቦችን አስቀምጧል። ኤአይ በተለያዩ የዓለም ቋንቋዎች እንዲሰራ፣ የሚጠቀመው ማህበረሰብ ፍላጎትና መረጃ ታሳቢ እንዲደረግ እና ሰዎች ቴክኖሎጂውን በብቃት መጠቀምና መገምገም እንዲችሉ በእውቀትና ተደራሽነት ላይ መስራት ናቸው።
ከሚመደበው አንድ ቢሊዮን ዶላር 40 በመቶ ለትምህርት፣ 40 በመቶ ለጤና፣ 10 በመቶ ለግብርና እና 10 በመቶ ለዲጂታል መሠረተ ልማት እንደሚውል ተገልጿል። በትምህርት ዘርፍ የኤአይ የትምህርት መሳሪያዎችን ለማስፋፋት፣ በጤና ዘርፍ የበሽታ ምርመራና የሕክምና ውሳኔ ድጋፍን ለማጠናከር፣ በግብርና ዘርፍደግሞ አርሶ አደሮች ከአፈር፣ ከአየር ሁኔታና ከሰብል ይዞታ ጋር የተጣጣመ የኤአይ ምክር እንዲያገኙ ለማስቻል ይውላል።
የጌትስ ፋውንዴሽን ሊቀመንበር ቢል ጌትስ ኤአይ ለሰው ልጆች ጥቅም እንዲውል ኩባንያዎች፣ መንግስታት እና የበጎ አድራጎት ተቋማት በጋራ መሥራት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute