የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ለመስራት ተስማሙ።
· MOU
EAII and Wollega University Sign MoU to Advance AI Research, Capacity Building, and Technology Development
ስምምነቱን አስመልክተዉ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ካስፈለገ በጋራ መስራት ትክክለኛ ዉሳኔ መሆኑን ገልጸዋል። በተደረገዉ ስምምነት መሰረት የኤ.አይ ቴክኖሎጂ ልማት፣ የሰው ኃይል ማብቃት እና የቴክኖሎጂዉ አስቻይ መሠረተ ልማቶችን በጋራ ለመጠቀም እንደሚሰራ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ም/ፕሬዚዳንት ድሪባ ዳባ (ዶ/ር) በበኩላቸዉ የአፕላይድ ዩኒቨርሲቲ የሆነዉ የኒቨርሲቲያቸዉ ለምርምርና ማስተማር ስራዉ ከሚያስፈልጉት መሰረታዊ ነገሮች አንዱ ኤ.አይ መሆኑን ገልፀዋል። በዚህም ቴክኖሎጂዉን ከመመራመር ባሻገር አገልግሎት ላይ ለማዋል ስምምነቱ መሰረት እንደሚሆን በንግግራቸዉ ጠቅሰዋል።
ሁለቱ ተቋማት በቀጣይም በተለያዩ መስኮች በጋራ የመስራት ፍላጎት እንዳላቸዉ በስምምነቱ ላይ ተመላክቷል። ስምምነቱ በኤ.አይ ዙሪያ የምርምር ስራዎችን እና ስልጠናዎችን በጋራ ለማካሄድ፣ የዘርፉን መሠረተ ልማቶች በትብብር ለማልማት እና ለመጠቀም ያለመ ነው፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute