የኢንዱስትሪ ዲጂታላይዜሽን እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ላይ ትኩረቱን ያደረገ የውይይት መድረክ ተካሄደ።
· Other
EAII Participates in Ethiopia Tamrit Expo Panel on AI and Industrial Digitalization to Drive Productivity and Economic Growth
በአዲስ ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት የውውይት መድረክ ተካሂዷል።
ውይይቱም የኢንዱስትሪ ዲጂታላይዜሽን እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን በኢንዱስትሪው መስክ መጠቀም የሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ነው።
በውይይት መድረኩ ተገኝተው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የዋና ዳይሬክተር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እና የቴክኖሎጂ አማካሪ ሻምበል ይልማ (ዶ/ር) ቴክኖሎጂው ለኢንዱስትሪው ዘርፈ ብዙ ችግሮች የተሻለ መፍትሄ ይዞ መምጣቱን ጠቁመዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱም የኤ.አይ መሰረተ ልማት በመገንባት እና ለኢንዱስትሪው ዘርፍ ቁልፍ የሆነውን በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት በትኩረት እየሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በኢትዮጵያ ለሚታየው የኢንዱስትሪው ዘርፍ ችግሮች ኤ.አይ እና ዲጂታላይዜሽን የመፍትሄው አካል መሆን እንደሚገባቸውና ዘርፉም በዚህ መልክ መቃኘት እንደሚገባው በፓናል ውይይቱ ተነስቷል፡፡ ቴክኖሎጂውንም ለመጠቀም አስቻይ ሁኔታዎችን መዘርጋት ላይ ትኩረት መደረግ እንደሚገባው በመድረኩ ተጠቁሟል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute