የዴንማርክ ልዑካን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ፡፡
· Visiting
Danish Delegation Visits EAII to Explore Artificial Intelligence Cooperation and Strengthen Ethiopia–Denmark Technology Partnerships
የልዑካን ቡድኑ በጉብኝቱ የኢንስቲትዩቱን የተለያዩ የስራ ክፍሎች ተዘዋዉረዉ ተመልክተዋል። በዚህም ኢትዮጵያ ለዘርፉ የሰጠችዉ ትኩረት እንዲሁም የተመዘገቡ ስኬታማ ስራዎችን ጎብኝተዋል። በተለይም ለማህበረሰብ ተጠቃሚነት በጤና፥ በግብርና ፥ በትምህርት፥ በመንግሥት አገልግሎቶች ማዘመን እና በስማርት ሲቲ ግንበታ በኩል የተመዘገቡ ስኬቶችን ልዑካን ቡድኑ አድንቀዋል።
የኢንስቲትዩቱ የዋና የዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊና የቴክኖሎጂ አማካሪ ሻምበል ይልማ (ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱ በተለያዩ ዘርፎች እያከናወናቸው ያሉትን ስራዎች በተመለከተ ለጎብኝዎቹ ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡ ልዑካኑ የኢንስቲትዩቱን የስራ እንቅስቃሴ ከጎበኙ በተጨማሪ ሁለቱ ሀገራት በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ዘርፍ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute