በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ተባባሪነት የተዘጋጀው "አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቃ።
· Other
New Amharic Book Explores AI’s Opportunities, Applications, Risks, and Connection to Human and Social Life
በቴክኖሎጂ አማካሪ እና የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሰለሞን ሙሉጌታ ካሳ የተጻፈውና"አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ" በሚል ርዕስ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀው መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል። በሳይንስ ሙዚየም የተመረቀው መጽሐፉ ስለኤ.አይ ቴክኖሎጂ ምንነት ብሎም በተለያዩ ዘርፎች የሚኖረውን አበርክቶ እና ስጋቶች
ዳሷል።
በምርቃ መርኃግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተርታዬ ግርማ (ዶ/ር) የኤ.አይ ቴክኖሎጂ የዘመኑ እውነታ
መሆኑን ተረድቶ በተጠና መንገድ ለመጠቀም ይቻል ዘንድ ይህመጽሐፍ ሊነበብ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ስለ መጽሐፉ ገለጻ ያደረጉት ዶ/ር ምህረት ደበበ በኩላቸው መጽሐፉ ቴክኖሎጂውን በተለያዩ መነጽሮች ለማየት እንደሚያግዝ ገልጸው፤ ከሰው ልጆች አዕምሮና ማህበራዊ ህይወት ጋር ያለውን ቁርኝት አስረድተዋል።
የመጽሐፉ ደራሲ ሰለሞን ሙሉጌታ ካሳ ለስኬቱ ድጋፍ ላደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና ለተባባሩ አካላት ምስጋናውን አቅርቧል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute