የኑክሌር ኃይል ለኤአይ እድገት፦ ለኢትዮጵያ ምን ትምህርት አለው?
· Other
Reliable and Clean Energy Emerges as a Foundation for AI Growth in the United States and Ethiopia
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እያደገ ሲሄድ አንድ ጥያቄ ወሳኝ እየሆነ መጥቷል፤ለኤአይ ዘርፍ የሚያስፈልገው ኃይል ከየት እናገኛለን ይህን ለመመለስ በአሜሪካ
የተዘጉ ሦስት የኑክሌር ጣቢያዎችን (ፓሊሳዴስ፣ ክሬንና ዱዌን አርኖልድ) ስራ ለማስጀመር መንግስት 4.42 ቢሊዮን ዶላር ብድር ለግሉ ዘርፍ በማዘጋጀት ወደ ስራ ገብቷል። ጣቢያዎቹ ሲመለሱ 2.25 ጊጋዋት ኃይል ያመነጫሉ። ዋናው ጥቅማቸው ያለማቋረጥ ማመንጨታቸው ነው፤ የኤአይ መረጃ ማዕከላት ደግሞ
በትክክል ይህንን ይፈልጋሉ።
ኢትዮጵያም የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን የዲጂታል ሽግግሩ ቁልፍ አድርጋ እየሰራች ነው፡፡ የኤአይ እድገቱ ከሌሎች ግብዓቶች እኩል የኃይል
አቅርቦቱንም በመሠረታዊነት ይፈልጋል። ኢትዮጵያ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ፣ ከሌሎቹ የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫዎች፣ ከነፋስና ከፀሐይ ኃይል የምታገኘው ንጹሕ ኤሌክትሪክ ትልቅ ዕድል ነው። ሌላ አማራጭ ሆኖ እየመጣ ያለው የኑክሌር ኃይልም የማይተካ ሚና አለው፡፡
ይህን ኃይል ከዘመናዊ መረጃ ማዕከላት፣ ከፈጣን ኢንተርኔትና ከወጣት የሰው ኃይል ጋር በማስተሳሰር ሀገራችን የአፍሪካ የኤአይ ማዕከል እንድትሆን እየተሰራ ነው።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute