የብሩንዲ የአዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ልዑካን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ።
· Visiting
Burundian Command and Staff College Delegation Visits EAII to Enhance Strategic Collaboration and Institutional Productivity
በብሩንዲ የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ አዛዥ ኮሎኔል ጆናስ ሳቡሽሚኬ የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኘ።
የኢንስቲትዩቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ዘውዴ ኢንስቲትዩቱ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በተለያዩ ዘርፎች ኤ.አይን መሰረት አድርጎ
የሰራቸውን ስራዎች በተመለከት ለጎብኚዎቹ ገለፃ አድርገዋል፡፡ ዳይሬክተሩ በገለፃቸው ኢንስቲትዩቱ በስማርት ሲቲ ግንባታ እንዲሁም በወንጀል መከላከል ረገድ ያለማቸውን ሲስተሞች በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ጎብኚዎቹ በበኩላቸው በኢንስቲትዩቱ ለተደረገላቸው አቀባበልና ገለፃ አመስግነው፤ በኤ.አይ ላይ ለመስራት የነበራቸውን ፍላጎት ይበልጥ የሚያጠናክሩ ስራዎች
በኢንስቲትዩቱ በማየታቸው መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ በዘርፉ ከአፍሪካ ቀዳሚ የሚያደርገውን እና ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ መሆን የሚያስችለውን ስራ እየሰራ ስለመሆኑ መመልከታቸውን
ልዑካኑ ገልጸዋል፡፡ በጤና፣ በግብርና፣ በፋይናንስ፣ በወንጀል መከላከል እንዲሁም በአገልግሎት ዘርፎች የተሰሩ ስራዎች የሚደነቁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute