“ኢትዮጵያ በኤ.አይ ላይ እየሰራች ያለችው ስራ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት መንገድ አመላካች እና አርዓያ የሚሆን ነው፡፡” የላይቤሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
· Visiting
Liberian Foreign Minister Says Ethiopia’s AI Initiatives Set a Model for Africa’s Economic Growth and Digital Productivity
በላይቤሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳራ ቤይሶሎው ኒያቲ የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝቷል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) የልዑካን ቡድኑን ተቀብለው ኢንስቲትዩቱ ተቀብለው ኢንስቲትዩቱ ስለሚሰራቸው ስራዎች ገለፃ አድርገዋል። በገለፃቸው ኢንስቲትዩቱ የማህበረሰቡን ችግሮች ለመፍታት በዘርፉ ከጥናትና ምርምር ጀምሮ የሰራቸውን በርካታ ተግባራት በተመለከተ ማብራሪያ አቅርበዋል። ኢንስቲትዩቱ በአህጉራዊ ትብብር ላይ በትኩረት እንደሚሰራና ተሞክሮዎቹን ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለማካፈል ዝግጁ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አረጋግጠዋል።
የላይቤሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳራ ቤይሶሎው ኒያቲ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በኤ.አይ ዘርፍ እያከናወነች ያለውን ተግባር በማድነቅ፤ ይህ ስኬት ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በተለይም ለላይቤሪያ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን ጠቁመዋል። እኛ የምንቆመው ለተሻለች ላይቤሪያ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፤ ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያን ምርጥ የኤ.አይ የቴክኖሎጂ ተሞክሮ እንደ አርዓያ እንወስዳለን ብለዋል፡፡
ሚንስትሯ ኢትዮጵያ በኤ.አይ ላይ እየሰራች ያለችው ስራ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት መንገድ አመላካች እና አርአያ መሆኑን ገልፀው፤ ቴክኖሎጂው ለአህጉሪቷ እድገት ዋስትና እንዲሆን በትምህርት ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ላይ ዙሪያ አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑ ተመላክቷል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute