በሰው ሠራሽ አስተውሎት ላይ እንዲህ ያለ የዕድገት ደረጃ በአፍሪካ ውስጥ አይተው እንደማያውቁ የተለያዩ ሀገራት የጤና ሚኒስትሮች ገለፁ፡፡
· Visiting
Participants of the 76th WHO Regional Committee for Africa visited the Ethiopian Artificial Intelligence Institute, praising Ethiopia’s progress in AI and highlighting opportunities for African countries to collaborate in health innovation, research and digital transformation.
የ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ኮሚቴ ጉባኤ ተሳታፊ የሆኑ የተለያዩ አገራት የጤና ሚኒስትሮች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኝተዋል። ጎብኝዎቹ በሰው ሠራሽ አስተውሎት ላይ እንዲህ ያለ የዕድገት ደረጃ በአፍሪካ ውስጥ አይተው እንደማያውቁ ገልፀው ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም ከኢንስቲትዩቱ ብዙ የሚማሩት ነገር እንዳለ አስገንዝበዋል።
ኢትዮጵያ በአስደናቂ ሁኔታ አቅሟን አሳይታለች ያሉት የጤና ሚኒስትሮቹ፤ ኢንስቲትዩቱ የሚሰራቸው የፈጠራ ሥራዎች ራዕዩን እንደሚያሳይ ተናግረዋል።
ሁሉንም ነገር ማግኘት ወደምንችልበት ደረጃ ለመድረስ እንደ አፍሪካ አንድ ላይ መሰብሰብ እና ከኢትዮጵያ ልምድ መውሰድ አለብን ያሉት ጎብኝዎቹ ሌሎች የአፍሪካ አገራት እና የጤና ሚኒስትሮች ከኢንስቲትዩቱ ጋር በስፋት እንዲገናኙና እንዲተባበሩ አሳስበዋል፡፡
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) በጤና፣ በግብርና እና በሌሎች ዘርፎች እየተመዘገበ ያለውን የምርምር እና ልማት ስኬት አስመልክተው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በገለጻቸውም ኢንስቲትዩቱ የአፍሪካ የልህቀት ማዕከል እንደመሆኑ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ
መሆኑን አንስተዋል። በተጨማሪም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ግዙፍ ዳታ ሴንተር በመገንባት ለተለያዩ ተቋማት እየሰጠ ያለው የክላውድ አገልግሎት፣ ስለ
ኤአይ ብሔራዊ ፖሊሲ፣ ለስታርታፖች ስለሚደረገው ድጋፍ ለጎብኚዎቹ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute