በወሳኝ የፋይናንስ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚሰነዘሩ የሳይበር ጥቃቶች ክፍያዎችን፣ ብድርን እና በገበያው ላይ ያለውን እምነት ሊያስተጓጉሉ እንደሚችሉ የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) አስጠነቀቀ።
· Other
IMF Warns Advanced Cyberattacks Could Threaten Global Financial Stability and Customer Trust
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ባንኮችን፣ የክፍያ ሥርዓቶችን እና ሌሎች ዋና ዋና የፋይናንስ አገልግሎቶችን ኢላማ የሚያደርጉ የተራቀቁ የሳይበር ጥቃቶች ከባድ መዘዝ ሊያስከትሉ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል። እንደዚህ ያሉ ጥቃቶች የክፍያ ሂደትን ሊያስተጓጉሉ፣ የብድር ተደራሽነትን ሊገድቡ፣ የደንበኞችን እምነት
ሊጎዱ እና በፋይናንስ ገበያዎች ላይ ያለውን መተማመን ሊያዳክሙ ይችላሉ ብሏል።
ባንኮች፣ የክፍያ አገልግሎት አቅራቢዎች እና የፋይናንስ ገበያ ሥርዓቶች እርስ በርስ በጥብቅ የተሳሰሩ በመሆናቸው በአንድ ዋና ተቋም ወይም የመሠረተ ልማት አቅራቢ ላይ የሚሰነዘር የተሳካ ጥቃት በመላው ሥርዓቱ ውስጥ በፍጥነት ሊሰራጭ እንደሚችል ተናግሯል።
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የፋይናንስ ተቋማትና ተቆጣጣሪዎች የሳይበር ደህንነት መከላከያዎችን እንዲያጠናክሩ፣ የአደጋ ምላሽ እቅድ እንዲያወጡ፣ የአደጋ መረጃን እንዲያጋሩ እና ሊከሰቱ ለሚችሉ የአሠራር መስተጓጎሎች ቀድመው አንዲዘጋጁ አሳስቧል። የፋይናንስ መረጋጋትን ፣የደንበኞችን እምነት ለመጠበቅ እና የሳይበር ክስተቶች ወደ ሰፊ የኢኮኖሚ ቀውሶች እንዳይሸጋገሩ ለመከላከል ጠንካራ የሳይበር ጥቃንትመቋቋም ከመቸውም ጊዜ በላይ አሁን አስፈላጊ መሆኑን
አፅንዖት ሰጥቶ በተራቀቁ የኤአይ ሞዴሎች የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን የበለጠ በተራቀቀና ደህንነቱ በተጠበቀ የኤአይ ሞዴል መከላከል እንደሚገባ ማሳሰቡን የዘገበው ዘ ኢኮኖሚክ ታይምስ ነው፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute