በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቁት እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለጉምሩክ ኮሚሽን ያለማቸውን ሥርዓቶች በዝርዝር እናስተዋውቃችሁ፡፡
· AI Solutions
Ethiopian AI Institute Unveils Advanced Digital Systems to Modernize Customs Operations, Enhance Efficiency, and Strengthen Border Security.
1.የኢትዮጵያ ኤሌክትሮኒክ ካርጎ መከታተያ ሥርዓት፡- የጭነቶችን አጠቃላይ የጉዞ ሂደት በቅጽበት (real-time) ቁጥጥር እና ትንተና እንዲደረግባቸው በማስቻል ከመነሻ እስከ መዳረሻቸው ለመከታተል እና ለመቆጣጠር የሚያገለግል የድረ-ገጽ እና ሞባይል መተግበሪያን ያካተተ ሥርዓት ነው፡፡ ሥርዓቱ በሦስት ቁልፍ ግብዓቶች ማለትም ሶፍትዌር፣ የማዘዣ/ መቆጣጠሪያ ማዕከል እና መሠረተ ልማት ተዋቅሯል።
ጭነቶችን በተመለከተ ምላሽ መስጠት (Respond)፣ ማሳወቅ/ማስጠንቀቅ (Notify/Alert)፣ መቆጣጠር (Monitor)፣ መከታተል (Track) እና የጭነቶችን አሁናው አድራሻ መጠቆም (Locate) ደግሞ አገልግሎቶቹ ናቸው።
2. ስማርት የጉምሩክ የድንበር ቁጥጥር እና አስተዳደር ሥርዓት፡- ሕገ ወጥ ድንበር ተሻጋሪ የንግድ እንቅስቃሴን (ኮንትሮባንድ) ለመቆጣጠር ያስችላል፡፡ በመስክ ስራዎች፣ በኬላዎች እና በማዕከላዊ የመቆጣጠሪያ ማዕከላት መካከል አሁናዊ ግንኙነትን በማስቻል በቴክኖሎጂ የተደገፈ የኮንትሮባንድ ቁጥጥር ሥርዓትን መዘርጋት ያስችላል፡፡ በተጨማሪም ዜጎች በቻትቦት ወይም በበይነመረብ አማካኝነት ኮንትሮባንድን የተመለከቱ ጥቆማዎችን ምስጢራዊነታቸው ተጠብቆ እንዲሰጡ ያስችላቸዋል፡፡
3. የመንገደኞች ስጋት አስተዳደር ሥርዓት፡- በአውሮፕላን የሚገቡ መንገደኞችን የጉዞ ታሪክ በመመርመር የጉምሩክ ፍተሻን የሚያቀላጥፍ ሥርዓት ነው፡፡ ዲጂታል የሻንጣ ክትትልን በመተግበር ቀልጣፋ የመንገደኞች ፍሰትንም ያረጋግጣል።
4.የጉምሩክ መጋዘንና ወኪሎች የፍቃድ አስተዳደር ሥርዓት፡- የዚህ ሥርዓት አስፈላጊነት የኮሚሽኑ ደንበኞች ጊዜ እና ቦታ ሳይገድባቸው በበይነ መረብ አማካኝነት የተቋሙን አገልግሎቶች እንዲያገኙ ማስቻል ነው፡፡ ይህ ሥርዓት በቻትቦት (በውይይት መለዋወጫ ሮቦት) ድልድይነት ሳምንቱን ሙሉ፤ ለ24 ሰዓት ያለምንም መዘግየት የደንበኞች አገልግሎትን ማቅረብ ያስችላል፡፡
ሥርዓቱ ኮሚሽኑን የተመለከቱ ወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለደንበኞች በአራት የቋንቋ አማራጮች አቅርቧል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute