የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘት ጉብኝት አድርጓል፡፡
· Visiting
Fostering Cooperation Between Faith Leaders and AI Innovators
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ የኢንስቲትዩቱን ስራዎች በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል፡፡ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በገለጻቸው ኢንስቲትዩቱ በሀገራችን የተለያዩ ዘርፎች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ የኤ.አይ ቴክኖሎጂዎችን እያለማ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ
በበኩላቸው የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በየጊዜው እራሱን እያዘጋጀ እና እያሳደገ በመምጣት ዓለም የደረሰችበት ደረጃ ለመድረስ እና አብሮ ለመጓዝ የሚያስችለው ቁመና ላይ መሆኑን በጉብኝቱ መገንዘብ መቻላቸውን ገልፀዋል፡፡ ከሃይማኖት ተቋማት ጋር በተለይም በግጭት አፈታት እና ቅድመ መከላከል ላይ የሚያግዙ ሥርዓቶችን ለማልማት እንዲቻል ጉብኝቱ በር የከፈተ ስለመሆኑ ጠቅላይ ፀሐፊው አንስተዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute