ኢትዮጵያ ለሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት ልዩ ትኩረት በመስጠት በአሜሪካን ሀገር እየተደረገ ባለዉ የሰሌክት ዩ.ኤስ.ኤ ኢንቨስትመንት ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነዉ።
· Other
EAII Represents Ethiopia at SelectUSA Investment Summit to Advance AI Partnerships, Investment Opportunities, and Global Competitiveness
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በዘንድሮው የሴሌክት ዩ.ኤስ.ኤ የኢንቨስትመንት ጉባኤ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡
በጉባዜዉ ኢትዮጵያ በዘርፉ እያከናወነች የሚገኘውን የምርምር፥ ልማትና እና ትግበራ ስራዎች በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) አማካኝነት ለተሳታፊዎች ማብራሪያ ቀርቧል፡፡ ይህ ጉባኤ ለኢንስቲትዩቱ በኤ.አይ እና ሌሎች በፍጥነት በማደግ ላይ ከሚገኙ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ውስጥ ቀጥተኛ ተሳትፎ ካላቸው አጋሮች ጋር ለመገናኘት እድል ፈጥሮለታል።
ኢንስቲትዩቱ በከፍተኛ የስራ ኃላፊው ደረጃ ያደረገው ይህ ተሳትፎ ኢትዮጵያ በኤ.አይ ዘርፍ ዓለማቀፍ ትብብሮችን ለማጠናከር እድል ፈጥሮላታል። በተጨማሪም የኢንቨስትመንት እድሎችን ለመዳሰስ እንዲሁም ሀገራችንን በዓለማቀፉ የኤ.አይ ሥነ-ምህዳር ውስጥ ለማስቀመጥ ያለመ ነው።
ጉባኤዉ ተቋማት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጅ ፍላጎት እና ትግበራቸውን እንዲያሳድጉ የሚያስችል ዋና መድረክ ሆኖ ያገለግላል። ፕሮግራሙ ከአሜሪካ መንግስት ባለስልጣናት፣ በስቴት ደረጃ የሚገኙ የኢኮኖሚ ልማት ድርጅቶች እና ከኢንዱስትሪ አጋሮች ጋር ቀጥተኛ የተሳትፎ እድሎች የተመቻቹበት ነው፡፡ ጉባኤው ለሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ኢንዱስትሪ ትኩረት የሚሰጡ ልዩ ክፍለ-ጊዜዎችን በማካተት በአሜሪካ ፤ ሜሪላንድ እየተካሄደ ነዉ።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute