የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ።
· Visiting
Officials and employees of the Commercial Bank of Ethiopia (CBE) visited the Ethiopian Artificial Intelligence Institute to observe its technological initiatives and explore opportunities for collaboration to advance the finance sector through AI-driven innovation.
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች የኢንስቲትዩቱን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ በጉብኝቱ ወቅት የኢንስቲትዩቱን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ሀገሪቱን ከኤ.አይ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ለማድረግ በተለያዩ ዘርፎች እየሰራቸው ስለሚገኙ ስራዎች ገልጸዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ለሚሰራቸው ስራዎች አድናቆታቸውን ያቀረቡት የባንኩ የስራ ኃላፊዎች፥ በኢንስቲትዩቱ የሚገኘው የቴክኖሎጂ አቅም የባንኩን ብሎም የፋይናንስ ዘርፉን ወደፊት ማራመድ የሚችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በኢንስቲትዩቱ የሚገኙትን የሮቦቲክስ ወርክሾፕ፣ የስታርታፕ ማዕከል እና የምርት ማሳያ ክፍልን በጉብኝታቸው ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
ከጉብኝቱ ጎን ለጎን በሁለቱ ተቋማት መካከል የሀገሪቱን የፋይናንስ ዘርፍ በቴክኖሎጂ ማዘመን እና በጋራ መስራት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute