ሩዋንዳ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዘ የሕክምና አገልግሎት ልትጀምር ነው፡፡
· AI Solutions
Rwanda to pilot AI technologies in health facilities to address medical staff shortages and improve care delivery.
የጌትስ ፋውንዴሽን በአፍሪካ የሚገኙ 1,000 ክሊኒኮችን ለመደገፍ ባወጣው አዲስ መርሓ-ግብር መሠረት ሩዋንዳ ከ50 በላይ በሚሆኑ የጤና ተቋሞቿ ውስጥ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሚሰሩ የጤና ቴክኖሎጂዎችን ለመሞከር መዘጋጀቷ ተገለጸ።
የሩዋንዳ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሥልጣን አንድሪው ሙሂሬ ለአሶሺየትድ ፕሬስ እንደተናገሩት የሕክምና አገልግሎትን የሚያቀላጥፍ፣ አስተዳደራዊ ጫናዎችን የሚቀንስ እና ባለሙያዎች ትክክለኛና ፈጣን ውሳኔዎችን እንዲያስተላልፉ የሚረዳ ትልቅ ዕድል ነው።
በአሁኑ ወቅት ሩዋንዳ ላሏት አንድ ሺህ ታካሚዎች አንድ የጤና ባለሙያ ብቻ የሚገኝ ሲሆን ይህም ዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ለአንድ ሺህ ታካሚ 4 ባለሙያዎች እንዲኖሩ ካስቀመጠው መስፈርት አንፃር እጅግ ያነሰ ነው።
እንደ አፍሪካን ኒውስ መረጃ የጌትስ ፋውንዴሽን እና ኦፕን ኤ.አይ "ሆራይዘን 1000" የተሰኘ አዲስ ፕሮጀክት ይፋ ያደረጉ ሲሆን ለዚህም በሁለት ዓመት ውስጥ አገልግሎት ላይ የሚውል 50 ሚሊዮን ዶላር በጋራ መመደባቸው የሚታወስ ነው።
ፕሮጀክቱም ከፍተኛ የጤና ባለሙያ እጥረት ባለባቸውና የመሠረተ ልማት ዝርጋታቸው ደካማ በሆኑ አገራት ውስጥ ኤ.አይ ጥራት ያለው ሕክምናን ተደራሽ ለማድረግ 'የጨዋታ ቀያሪ' ሚና ሊኖረው ይችላል ተብሏል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute