የሕንድ ስታርትአፕ የሆነው አቫታር ኤአይ የህንድን ባህልና ወግ መረዳት የሚችል ቫርያ የተሰኘ አዲስ የቪዲዮ ማመንጫ ሞዴል ይፋ አደረገ።
· AI Solutions
India Unveils Varya AI Video Model to Accelerate Affordable AI Innovation, Digital Creativity, and Global Competitiveness
ሞዴሉ በአሊባባ ዋን 2.2 ላይ ተመስርቶ በ"ዲስቲሌሽን" ቴክኖሎጂ የተገነባ ሲሆን ከተለመዱት የኤአይ ሞዴሎች በ10 እጥፍ ፍጥነት ቪዲዮ ማመንጨት ይችላል። ለምሳሌ፤ ባለ 5 ሰከንድ ቪዲዮን በ45 ሰከንድ ውስጥ ብቻ ያጠናቅቃል።
የአገልግሎት ክፍያውም እንደ ቪዮ፣ ክሊንግ፣ ሉማ እና ረንዌይ ካሉ ዓለም አቀፍ ሞዴሎች እጅግ በጣም ርካሽ ሲሆን ወደ 20 እጥፍ ገደማ የዋጋ ልዩነት አለው።
እንደ ቴክክራንች ዘገባ የምስል ማመንጫ ሞዴሎች ብዙውን ጊዜ የባህል ይዘቶችን ይሳሳታሉ እንዲሁም የተለመዱ ምስሎችን ያወጣሉ፤ አቫታር ኤ.አይ ግን ምግቦችን፣ አልባሳትን እና በዓላትን ጨምሮ የአገር በቀል ባህላዊ ይዘቶችን ጠንቅቆ እንዲለይ ቫርያንን ለማሰልጠን በጥንቃቄ የተመረጡ መረጃዎችን መጠቀም መቻሉ ተገልጿል።
የቫርያ መለቀቅ ሕንድ በትላልቅ ሞዴሎች ከመፎካከር ይልቅ አነስተኛ ወጪ ያላቸው እና ለህዝቡ በቀላሉ ሊደረሱ የሚችሉ የኤ.አይ መተግበሪያዎች ላይ ትኩረት ማድረጓን ያሳያል ተብሏል። ቫርያ በሕንድ መንግሥት የኤአይ ኮሽ (AI Kosh) ፖርታል ላይ በነፃ የሚለቀቅ በመሆኑ ማንኛውም አልሚ ለራሱ ፍላጎት ሊያሻሽለውና ሊጠቀምበት ይችላል።
ሕንድ እ.ኤ.አ. እስከ በ2028 የ200 ቢሊዮን ዶላር የኤ.አይ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ የጂፒዩ አቅሟን ከእጥፍ በላይ ለማሳደግ አልማለች።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute