የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ዲጂታል የሲቪል ምዝገባ እና ቫይታል ስታትስቲክስ (CRVS) ሥርዓት በይፋ ተመረቀ።
· AI Solutions
The AI-powered Digital CRVS System enhances civil registration and supports Ethiopia’s Digital Ethiopia 2030 strategy.
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ያለማው ዲጂታል የሲቪል ምዝገባ እና ቫይታል ስታትስቲክስ (CRVS) ሥርዓት በይፋ ተመርቋል። የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ሥርዓት የአንድን ሀገር ህዝብ ቁጥር፣ የህይወት ኩነቶች እና
የቤተሰብ መዋቅር በህጋዊ መንገድ ለመመዝገብ የተዘረጋ የቴክኖሎጂ የአሰራር ሥርዓት ነው። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር
ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱ እንደሀገር ለማሳካት የታለመውን የዲጂታል 2030 ራዕይ በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ታግዞ ዉጤታማ እንዲሆን የበኩሉን እየተወጣ
መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ ሥርዓት በሀገር ደረጃ እየታየ ያለዉ ለዉጥ ማሳያ ነዉ ሲሉም ገልጸዉታል። ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት የበመርኃ
ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር በጠንካራ መሰረት የተደገፈ ሥርዓት በመገንባት ረገድ የማይተካ ሚና አለው ብለዋል። በዚህም የሚመለከታቸዉ አካላት በሙሉ ለተፈጻሚነቱ እንዲሰሩ አሳስበዋል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ሥርዓቱን በአጭር ጊዜ ያለምንም ክፍያ በማልማት ለዚህ በማብቃቱ ልባዊ
ምስጋናቸዉን አቀርበዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በበኩላቸዉ ይህ ሥርዓት ሀገራዊ የቅንጅት ስራን በመዘርጋት ብልጽግናችንን ለማረጋገጥ ያስችላል ብለዋል። ኢንስቲትዩቱቀደም ሲል መሰል ሥርዓት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ ማስጀመሩ የሚታወስ ነዉ። በዕለቱ ችግኝ ተከላ እና በድሬዳዋ የሚገኘዉ የኢሚግ
ሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መ/ቤት የሚካሄዱ የዲጂታላይዜሽኝ ስራዎችን ጉብኝት ተካሂዷል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute