በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ አመራር እና አባላት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ፡፡
· Visiting
Special Operations Command Delegation Reviews EAII’s Advanced AI Capabilities and National Innovations
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ ለዕዙ አባላት አቀባበል በማድረግ ስለአዲሱ ዋና መሥሪያ ቤት እና ስለኢንስቲትዩቱ ኤ.አይ ተኮር ስራዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ በሕግ ማስከበር፣ በጤና፣ በግብርና፣ በፍትሕ እና ሀገርኛ ቋንቋዎችን የማሽን መገልገያ ቋንቋ ለማድረግ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ተጠቅሞ እየሰራቸው ስለሚገኙ ስራዎች ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ አቅርበዋል፡፡
የዕዙ አባላት በጉብኝታቸው የሮቦቲክስ ወርክሾፕ፣ ዲጂታል ቤተ መጻሕፍት፣ የስታርታፕ ማዕከል እንዲሁም የምርት ማሳያ ክፍልን ተመልክተዋል።
ከጉብኝቱ በኋላ የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ አባላቱ በሰጡት አስተያየት በኢንስቲትዩቱ የተመለከቱት የቴክኖሎጂ አቅም ከጠበቁት በላይ መሆንኑ ገልጸዋል፡፡ ይህም የስራ ተሞክሮ እና እውቀት እንዲቀስሙ ከማስቻሉ ባሻገር ሀገራዊ የቴክኖሎጂ እድገቱ ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በተግባር ለማየት የቻሉበት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute