በኢትዮጵያ የአርሶ አደሮችን ምርታማነት ለማሳደግ እና የግብርናውን ዘርፍ በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ለመደገፍ ያለመ የምክክር መድረክ ተካሄደ።
· Education
AI in Agriculture Workshop in Ethiopia Highlights Potential to Boost Farmer Productivity and Generate $3.5 Billion Annual Income
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ ግብርና ሚነስቴር፣ የኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት እና በቢል ኤንድ ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን አዘጋጅነት በተከናወነው በዚህ መድረክ የዘርፉ ተመራማሪዎች ኤ.አይ በግብርና ዘርፍ ያለውን ሚና በሚመለከት መክረዋል፡፡
በመድረኩ ላይ በቀረበው ጥናት መሰረት በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ኤ.አይን 20 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ገበሬዎች መጠቀም ቢጀምሩ የአርሶ አደሩን ገቢ በዓመት 3.5 ቢሊዮን ዶላር የማሳደግ አቅም እንዳለው ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም በቴክኖሎጂው በታገዘ የምክር አገልግሎት የምርት ጥራትና መጠንን እስከ 70 በመቶ በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ እንደሚቻል ተመላክቷል።
ኤ.አይ መረጃዎችን በተለያዩ የሀገራችን ቋንቋዎች በድምፅ እና በጽሁፍ ለአርሶ አደሩ ለማድረስ፣ የእንስሳትና የሰብል በሽታዎችን አስቀድሞ ለመለየት፣ ድርቅና መሰል አደጋዎችን ለመተንበይ እንደሚያስችል ተገልጿል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን እየሰራቸው የሚገኙ ስራዎች በመድረኩ ላይ ቀርበዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute