1.2 ቢሊዮን ወጣቶችና የኤአይ ተስፋ
· Other
Global AI Summit Explores How Digital Transformation Can Create Jobs and Opportunities for Youth
በሚቀጥሉት ከ10 እስከ 15 ዓመታት ውስጥ በታዳጊ አገራት የሚኖሩ 1.2 ቢሊዮን ወጣቶች የሥራ ገበያውን ይቀላቀላሉ። ይህ ቁጥር ብዙ ዕድል ያለው ቢሆንም
፣ለሁሉም ሥራ ማግኘት ትልቅ ፈተና ነው። ታዲያ ቴክኖሎጂን በአግባቡ ተጠቅመን እነዚህ ወጣቶች ሥራና ገቢ እንዲያገኙ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?
ይህ የዘመናችን ቁልፍ ጥያቄ ሆኗል።
ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመፈለግ ዓለም ባንክ ከደቡብ ኮሪያ መንግሥት ጋር በመተባበር ዓለም አቀፍ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና የዲጂታል ለውጥ ጉባኤ አዘጋጅቷል። ጉባኤው ቴክኖሎጂ ለኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለምርታማነት የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ ያጎላል።
ተሳታፊዎች በሦስት ዋና ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው፤ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተደራሽነትና ተመጣጣኝ ዋጋ፣ ለኤአይ ልማት የሚያስፈልጉ መሠረተ ልማቶች፣ እንዲሁም ኃላፊነት የተሞላበትና የሕዝብን እምነት የሚያተርፍ የኤአይ አጠቃቀም። ትኩረቱ ከንድፈ ሐሳብ ያለፈ ነው፤ በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በቱሪዝምና በመንግሥት አገልግሎቶች የኤአይ መፍትሔዎችን በመተግበር የአገልግሎት ጥራትን ማሻሻልና አዳዲስ የልማት ዕድሎችን ማስፋት ነው።
ጉባኤው መንግሥታትን፣ የልማት አጋሮችን፣ የግሉ ዘርፍ ተወካዮችን፣ ተመራማሪዎችንና ወጣቶችን በአንድ መድረክ አሰባስቧል። ዓላማውም ቴክኖሎጂው ለሰው ልጆችና ለኢኮኖሚ ዕድገት የበለጠ ጠቃሚ የሚሆንበትን መንገድ ማሳየት ነው።
ኢትዮጵያም ከዚህ ጉዞ ወደኋላ አልቀረችም። የዲጂታል ሽግግሩ እንዲሳካ በትምህርትና ሥልጠና ብቁ የሰው ኃይል እያፈራች ነው፤ አዳዲስ የፈጠራ ሐሳብ ያላቸውን ስታርታፖችንምትደግፋለች። ግቡም ወጣቶች በአገር ውስጥ ብቻ ሳይወሰኑ፣ በአህጉራዊና በዓለም አቀፍ የኤአይ ገበያ ላይ የራሳቸውን አሻራ እንዲያሳርፉ ማስቻል ነው።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute