ፕሬዚዳንት ትራምፕና የቴክኖሎጂ ግዙፎች የኤአይ ደህንነት ቃል ኪዳን ተፈራረሙ
· Other
Trump and Leading Technology Companies Unveil Voluntary Agreement to Strengthen AI Oversight, Independent Auditing, and System Security
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከግንባር ቀደም የቴክኖሎጂና የኤአይ ኩባንያዎች መሪዎች ጋር በፈቃደኝነትላይ የተመሠረተ የኤአይ ደህንነት ስምምነት በዋይት ሀውስ ይፋ አድርገዋል። ሮይተርስ እንደዘገበው በመድረኩ ላይ የOpenAI፣ Anthropic፣ Meta፣ Google እና Nvidia ከፍተኛ ኃላፊዎች
ተገኝተዋል።
ኩባንያዎች የሚያበለጽጓቸውን ሥርዓቶች በውስጥ ቁጥጥር መከታተል፣ ሥርዓቶቹ በተነደፉበት መንገድ ብቻ መሥራታቸውን በገለልተኛ ኦዲተሮች ማስመርመር እንዲሁም ኤአይ ያልተፈቀደ የቴክኒክ ሥርዓት እንዳይደርስ የደህንነት መከላከያዎችን ማጠናከር እንዳለባቸው በስምምነቱ ተደንግጓል።
ዋና ትኩረቱ የኤአይ ኤጀንቶች ያልተጠበቀ ባህሪ እንዳያሳዩና የዓለም አቀፍ የኤአይ ደህንነት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ መጠበቅ ነው። ትራምፕ አዲስ የፌዴራል
ደንብ ከማውጣት ይልቅ ኢንዱስትሪው ራሱን መቆጣጠሩ እንደሚሻል ተናግረዋል። በተጨማሪም የኤአይ ደህንነትን የሚከታተል ባለ10አባላት ኮሚቴ ለማቋቋም እያጤኑ መሆኑን ገልጸዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute