የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደረገበት።
· Other
EAII Director General Worku Gachena (PhD) presented the Institute’s performance report, highlighting full achievement of planned data targets, infrastructure development milestones, and continued contributions to Digital Ethiopia 2025 and preparations for Digital Ethiopia 2030.
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) የኢንስቲትዩቱን የስድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል። በሪፖርቱ የኢንስቲትዩቱ ስትራቴጂክ ግቦች፣ ፕሮጀክት አፈፃፀም፣ የኦዲት ስራዎች፣ የበጎ አድራጎት ስራዎች እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮች ተዳሰዋል።
ለኤ.አይ ቴክኖሎጂ ልማት የጀርባ አጥንት በሆነው ዳታ ማሰባሰብ እና ማጠናቀር ረገድ ሪፖርቱ በሚሸፍነው ጊዜ በትኩረት ስለመሰራቱ ተገልጿል። ይህም ከእቅድ አኳያ መቶ ፐርሰንት ስኬታማ መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል።
በስድስት ወራቱ ሪፖርት የኢንስቲትዩቱ ዋና መሥሪያ ቤት እና የስታርታፕ ማዕከል ግንባታ እና እድሳት እንደ ቁልፍ ተግባር ተገልጿል።
ኢንስቲትዩቱ ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅርበት በመስራት ኢትዮጵያ ከቴክኖሎጂው የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ የበኩሉን እየተወጣ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
ተቋሙ በሰው ኃይል አቅም ግንባታ እንዲሁም ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 መሳካት እና ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ዝግጅት ያበረከተው አስተዋጽኦ በጉልህ ተነስቷል።
የኢንስቲትዩቱ አመራር እና ሰራተኞች በሪፖርቱ ላይ ሀሳቦችን አንስተው ውይይት ተደርጓል።
ከሪፖርቱ በተጨማሪ የኢንስቲትዩቱ አመራር እና ሰራተኞች በአዲስ አበባ እየተሰሩ የሚገኙ የወንዝ ዳር ልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute