ሮክፌለርና ኦፕንኤአይ ለዘመናዊ ከተሞች ግንባታ የሚውል የ 50 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረጉ
· AI Investment
$50 Million Global AI Grant Program Launched to Transform Urban Public Services
የሮክፌለር እና የኦፕንኤአይ ፋውንዴሽን የከተሞችን የሕዝብ አገልግሎት በኤአይ ለማሻሻል 50 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ዓለም አቀፍ የድጋፍ ፕሮግራም ይፋ
አደረጉ።
“Cities Deliver: AI Solutions for Public Services” የተሰኘው ፕሮግራም ኤአይን በመጠቀም የከተሞችን አስተዳደር ዘመናዊ ለማድረግ፣
የነዋሪዎችን ፍላጎት ቀድሞ ለመለየትና የሕዝብ አገልግሎቶችን በፍጥነትና በጥራት ለማድረስ የሚሠሩ ብቁ ድርጅቶችን ይደግፋል። ፕሮግራሙ ለእያንዳንዱ ፕሮጀክት ከ500 ሺህ እስከ 2 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ በመስጠት እስከ 100 ሚሊዮን የከተማ ነዋሪዎችን ለመድረስ አቅዷል።
ድጋፉ በጤና፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በአካባቢ ጥበቃና የአደጋ መከላከል እንዲሁም በዜጎች ተሳትፎና በመንግሥት አገልግሎት ማሻሻል ላይ ያተኩራል። በብራዚል
ሪዮ ዴ ጄኔሮ የኤአይ የጎርፍ ማስጠንቀቂያ ሥርዓትን፣ በኮሎምቢያ የዴንጊ በሽታ ወረርሽኝን የሚተነብየውን Dengue.AI እና በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን የዲጂታል የነዋሪዎች ተሳትፎ መድረክን ማስፋፋት ከታቀዱት ሥራዎች መካከል ናቸው።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute