የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከስካይ ዊን ኤሮናቲክስ ኢንደስትሪ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ፡፡
· MOU
Sky Win Aeronautics Partners with EAII, Air Force, and Leading Institutions to Advance Ethiopia’s Drone Technology and Strengthen National Innovation Capacity.
ስካይዊን ኤሮኖቲክስ ኢንደስትሪ በሀገር ውስጥ ማምረት የጀመራቸውን ድሮኖች ምርት በማስፋት የድሮን ቴክኖሎጂን በምርምር እና ሥርፀት ለማሳደግ እንዲሁም ተግባራዊ ተሞክሮን ለማዳበር የሚያግዘውን ትብብር ለመፍጠር የሚያስችለውን ስምምነት ከተለያዩ ተቋማት ጋር ተፈራርሟል፡፡
ስምምነቱ የተፈረመው ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ ከኢፌዴሪ አየር ኃይል፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ከመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ ግሩፕ እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር ነው፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱን በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በኩል የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ ፈርመዋል፡፡
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ሲሳይ ቶላ በፊርማ መርሐ-ግብሩ ላይ እንደገለጹት፤ ብሔራዊ ጥቅምን ከማስከበር እንዲሁም ካለው የላቀ ኢኮኖሚያዊና ስትራቴጂያዊ ፋይዳ አንጻር የድሮን ቴክኖሎጂን በራስ አቅም ማልማት ወቅቱ የሚጠይቀው ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ስምምነቱ ስካይ ዊን ኤሮናቲክስ ኢንደስትሪ ከኢንስቲትዩቱ እና ከሌሎቹ ተቋማት ጋር ስትራቴጂክ አጋርነት ለመፍጠርና በምርምር፣ በፈጠራ፣ በእዉቀት ሽግግር እና በአቅም ግንባታ በጋራ ለመስራት እንደሚያስችለው ተመላክቷል፡፡
ከመግባቢያ ሰነድ ፊርማ መርሓ ግብሩ ባሻገር የስካይዊን ኤሮኖቲክስ ኢንደስትሪ አሁናዊ ሁኔታ እና የድሮን ምርቶቹ ጉብኝት ተደርጓል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute