ስፖቲፋይ ፍትሃዊ የአርቲስቶችን ተጠቃሚነት እና የዘፈን ደራሲያንን ልምድ የሚያረጋግጥ አዲስ የኤ.አይ ሞዴል ለማዘጋጀት የሚያስችለውን ስምምነት አደረገ፡፡
· AI Solutions
Spotify Partners with Major Labels to Develop Responsible AI Systems that Protect Artists’ Rights and Ensure Fair Creative Compensation.
የዓለማችን ትልቁ የበይነ መረብ የሙዚቃ እና ፖድካስቶች ማደመጫ መድረክ የሆነው ስፖቲፋይ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በኃላፊነት ለመጠቀም እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ተቋሙ ፍትሃዊ የአርቲስቶችን ተጠቃሚነት እና የዘፈን ደራሲያንን ልምድ ለማረጋገጥ አዲስ የኤ.አይ ሞዴል ለማዘጋጀት ከሶኒ፣ ዩኒቨርሳል እና ዋርነር ሚዩዚክ ጋር ስምምነት ማድረጉን አስታውቋል።
ስምምነቱ ኤ.አይን በኃላፊነት በመጠቀም የሥነ-ጥበብ ስራዎችን ለማዘጋጀት እና የአርቲስቶችን የቅጂ መብት ለማስከበር ያለመ ነው፡፡ ኩባንያው በስምምነቱ መሰረት ከመብት ባለቤቶች፣ አርቲስቶች እና የዘፈን ደራሲያን ጋር በመሆን በኤ.አይ ምርምር እና ልማት ላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት እናደርጋለን ብሏል።
ስፖቲፋይ ቴክኖሎጂ ሁልጊዜ አርቲስቶችን ማገልገል አለበት ብሎ እንደሚያምን እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የፈጠራ ስነምህዳርን እያሰፋ መሆኑን ገልጾ ወደ ተግባር የሚያስገባው የኤ.አይ ስርዓት አርቲስቶች፣ የፈጠራ መብት ባለቤቶች እና አከፋፋዮች ለስራዎቻቸው ተገቢውን ክፍያ እንዲያገኙ እንደሚያስችላቸው የቢ.ቢ.ሲ መረጃ ጠቁሟል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute