የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አዲሱን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና መስሪያ ቤት ጎበኙ።
· Visiting
Strengthening Collaboration for Digital Health Advancement
በጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሳህረላ አብዱላሂ የተመራ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ልዑካን ቡድን አባላት በኢንስቲትዩቱ ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) ተቋሙ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የጤናውን ዘርፍ ለማዘመን እየሰራቸው ስለሚገኙ ምርምሮች እና ስለአዲሱ ዋና መሥሪያ ቤት አጠቃላይ ገፅታ ገለጻ አድርገዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት ኢንስቲትዩቱ በጤናው ዘርፍ እየሰራቸው የሚገኙ ስራዎች ለጤና ሚኒስቴር ትልቅ አቅም እንደሚፈጥሩ በመግለፅ፤ ኢንስቲትዩቱ ሌሎች ተቋማትን በሚያግዝ መልኩ ተደራጅቶ በማየታቸው ትልቅ ኩራት እንደተሰማቸው ተናግረዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute