የአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ ልዑክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኘ::
· Visiting
The Ethiopian Artificial Intelligence Institute has graduated its first cohort of startups following six months of intensive training, mentorship and support designed to transform innovative ideas into market-ready solutions.
በአሜሪካ መንግሥት የመካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ምክትል ረዳት ሚኒስትር ማርክ ሚቸል የተመራ ከፍተኛ ልዑክ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የሥራ ጉብኝት አደረገ።
በጉብኝቱ ወቅት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ለልዑካን ቡድኑ ባደረጉት ገለፃ በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን የረጅም ዓመታት ታሪካዊ ግንኙነት በማስታወስ፤ ኢንስቲትዩቱ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ የሚያከናውናቸውን ዋና ዋና ተግባራት በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ በገለጻቸው ኢንስቲትዩቱ በሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት ቴክኖሎጂ ምርምር እና ልማት ስኬታማ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን አስተረድተዋል።
በተለይም በተፈጥሮ ቋንቋ ቅንብር የኢትዮጵያን ሀገር በቀል ቋንቋዎች ለማሽን በማስተማር ረገድ ሀገራችን ለልዩ ልዩ ተግባራት መጠቀም መጀመሯን አስረድተዋል። በተጨማሪም ስታርታፖችን ለመደገፍ ኢትዮጵያ በልዩ ትኩረት እሰራች እንደሆነ እና በትብብር አብሮ ለመስራት ምቹ ምህዳር መኖሩን ገለፀዋል።
በአሜሪካ መንግሥት የመካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ምክትል ረዳት ሚኒስትር ማርክ ሚቸል በበኩላቸው፣ ለተደረገላቸው አቀባበልና ገለጻ ምስጋና አቅርበው የኢንስቲትዩቱ እንቅስቃሴ ከጠበቁት በላይ መሆኑን ገልጸዋል። ኢንስቲትዩቱ ለስታርታፖች የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረትና የሚያደርገውን ድጋፍ ያደነቁት ሚኒስትሩ በሮቦቲክስ፣ በሆሎግራም ቴክኖሎጂ፣ በተፈጥሮ ቋንቋ ቅንብር እና በሌሎችም ዘርፎች ያከናወናቸው ተግባራት ለአርአያነት የሚበቁ ናቸው ብለዋል።
ከጉብኝቱ ጎን ለጎንም ሁለቱ ሀገራት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ሁኔታዎች ላይ ፍሬያማ ውይይት አካሂደዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute