BERT ምንድን ነው?
· AI Solutions
How Google’s BERT Technology Helps Search Engines Understand Language, Context, and User Intent
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ አድማስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ መጥቷል። ከማሳያዎቹ አብዛኛው ሰው ሳያውቀው የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ከተጠቀመባቸው መንገዶች አንዱ በጉግል (Google) ላይ መረጃዎችን ሲፈልግ (Search ሲያደርግ) ነው።
በጉግል በሚፈለጉ አጠቃላይ መረጃዎች ውስጥ ወደ 10% ገደማ የሚሆኑት BERT ( Bidirectional Encoder Representations from Transformers ) የተሰኘውን የኤአይ ስልተቀመር የሚጠቀሙ በመሆናቸው፤ ማንኛውም ሰው ሳያውቀው የዚህ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ሆኗል። ይህ ቴክኖሎጂ
ጉግል የቃላትን ትክክለኛ ቅደም ተከተል እና አውድ በተሻለ መንገድ እንዲረዳ በማድረግ ተጠቃሚዎች እንዴት እንደሚፈልጉ በግልጽ እንዲያውቅ አስችሎታል።
BERT ዘመናዊ ከሆኑ ትልልቅ የቋንቋ ሞዴሎች (Large Language Models - LLMs) አንዱ ሲሆን፤ የቃላትን ትክክለኛ ቅደም ተከተል፣ አውድ እና ውስብስብ የሰው ልጅ የንግግር ዘይቤዎችን በጥልቀት በመረዳት ረገድ ከፍተኛ አቅም ያለው የኤአይ ቴክኖሎጂ ነው።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute