አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዓይነ ሥውራን የራሳቸውን ገጽታ እንዲረዱ እያስቻለ ነው፡፡
· AI Solutions
AI-powered mirrors enhance independence by describing appearance and surroundings to visually impaired users.
“የኤ.አይ መስታወት” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይህ የኤ.አይ ቴክኖሎጂ ለዓይነ ስውራን የራሳቸውን ገጽታ እናአካባቢ እንዲገነዘቡ አዲስ መንገድ የከፈተ ነው።
ከእነዚህ ሥርዓቶች መካከል “Be My Eyes” የተባለው መተግበርያ ተጠቃሽ ነው፡፡ መተግበርያው የአንድን ሰው ምስል ለመተንተን እና በድምጽ ግብረመልስ ለመግለጽ የኮምፒዩተር ቪዥን እናአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ይጠቀማል። ከሌሎች ሰዎች አስተያየቶችን ለማግኘት ጥገኛ ከመሆን ይልቅ የመተግበርያው ተጠቃሚዎች የአለባበስ ምርጫቸውን፣ የፀጉር አሠራራቸውን፣ ወይም ፊታቸው የተስተካከለ ስለመሆኑ ፈጣን ግብረ መልሶችን ማግኘት ይችላሉ።
እንደ ቢ.ቢ.ሲ ዘገባ ከሆነ የዚህ ቴክኖሎጂ ዋና ጠቀሜታው ዓይነ ሥውራን ስለራሳቸው የየዕለት ገጽታ ለመረዳት በሰዎች ላይ ጥገኛ ከመሆን ተላቀው በራስ ግንዛቤ እናነፃነት ላይ እንዲመሰረቱ ማስቻሉ ነው፡፡ ለብዙዎች ከዚህ ቀደም ያልተጨበጠ ወይም በማህበረሰቡ ጣልቃ ገብነት ላይ የተመሰረተ የራስ ምስል ግላዊ ድምዳሜ ላይ ይደርሱ ነበር። አሁን ግን በዚህ ቴክኖሎጂ አማካኝነት ተጠቃሚዎች በራሳቸው ገጽታቸውን እንዲያስተካክሉ ያስችላቸዋል፡፡
የቴክኖሎጂው ዓላማ ዕይታን ወደነበረበት መመለስ ሳይሆን ለዓይነ ስውራን አዲስ አማራጭ በማቅረብ ለራስ ያለን ግንዛቤ እናማንነትን የሚያዩበትን መንገድ ለመቀየር ያስቻለ ነው፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute