አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በኢትዮጵያ የሕክምና ትምህርትን በማሳደግ፣ በጤና አገልግሎት እና በጥናትና ምርምር ያለው ሚና ላይ ያተኮረ ኮንፍረንስ ተካሄደ።
· AI Solutions
The 62nd Ethiopian Medical Association Annual Conference highlights the growing role of AI in healthcare, with the Ethiopian Artificial Intelligence Institute showcasing innovations to modernize medical services.
የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና ከሌሎች ተቋማት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ላይ ትኩረቱን ያደረገ 62ኛውን ዓመታዊ የሕክምና ኮንፍረንስ እያካሄደ ይገኛል፡፡ በሂልተን ሆቴል እየተካሄደ በሚገኘው ኮንፍረንስ ላይ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የዘርፉ ባለሞያዎች ታድመውበታል፡፡
በኮንፍረንሱ ላይ ጽሑፍ ያቀረቡት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) በሕክምናው መስክ ግዙፍ እውቀት ያካበቱ ምሁራን እውቀት ለኤ.አይ በማስተማር እውቀትን ለትውልድ ከማስተላለፍ ባለፈ በጤናው ዘርፍ ያሉ ችግሮችን መፍታት እና አገልግሎቱንም ማዘመን ይቻላል ብለዋል።
ኤ.አይን በጤና አገልግሎት ውስጥ መጠቀም የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን ግዴታ እየሆነ ነው ያሉት ዶ/ር ታዬ፥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመጓዝ በኤ.አይ ዘርፍ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰሃረላ አብዱላሂ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የበለፀጉ የኤ.አይ ስርዓቶችን በስፋት ለመጠቀም ብሎም ለማስፋፋት ጤና ሚኒስቴር ከኢንስቲትዩቱ ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን በኮንፍረንሱ ላይ ባደረጉት ንግግር አንስተዋል።
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የጤናውን ዘርፍ በማዘመን ያለው ቀዳሚ ሚና እና ተግባራዊ የሚሆንባቸው አስቻይ ሁኔታዎችን የፈተሸ ውይይት የመድረኩ ትኩረት ነበር።
ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ዓመታዊ ኮንፍረንስ ላይ ከውይይት በተጓዳኝ ጤና ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ምርት እና አገልግሎቶች ለእይታ ቀርበዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute