በኢንስቲትዩቱ ሲሰጥ የቆየዉ የፓን አፍሪካ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስታርታፕ ቡትካምፕ ፕሮግራም ስልጠና በስኬት ተጠናቀቀ።
· Education
Pan-African AI Startup Bootcamp Concludes with 51 Startups Equipped for Cross-Border Innovation
በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በሚገኘዉ የኤ.አይ ዩኒፖድ ለ51 አፍሪካዊያን ስታርታፖች ሲሰጥ የነበረዉ ስልጠና ማጠናቀቂያ መርኃ ግብር ተካሂዷል።
በስልጠና ማተናቀቂያ መርሓ ግብሩ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር ሰልጣኞችን በቆይታቸዉ ሳይንሳዊ እዉቀትንና ሙያዊ ልምዶችን እንደቀሰሙ፣ አዳዲስ ግንኙነቶችን እንደፈጠሩ እና ያላቸዉን የፈጠራ ሀሳቦችን ያዳበሩበት እንደነበር ገልጸዋል። በቀጣይም ይህን ፓን አፍሪካዊ በሆነ እይታ የተቃኘ ልምድ ወደ ገበያ በማዉጣት ድንበር ተሻጋሪ የሆነ ስራ እንዲሰሩ አሳስበዋል።
የዩ.ኤን.ዲ.ፒ ኢትዮጵያ ተወካይ ሳሙኤል ዶ (ዶ/ር) በበኩላቸዉ ዛሬ የሚመረቁት ስታርታፖች አፍሪካን በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ዉድድር ሜዳ የሚወክሉ ስራ ፈጣሪዎች እንደሚሆኑ ተናግረዋል። ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተዉጣጡት እነዚህ የኤ.አይ ስራ ፈጣሪዎች አህጉራችንን የሚያኮራ ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኙ በማንሳት መፍጠራቸዉን እንዲቀጥሉ አደራ ብለዋል።
በመዝጊያ መርኃ ግብሩ ላይ ልምዳቸዉን ያጋሩ ስታርታፖች ቆይታቸዉ የፈጠራ ዉጤቶቻቸዉን ያዳበሩበት፣የቴክኒካል ክህሎትን ያሳደጉበት፣አዳዲስ ትስስር የፈጠሩበት እንዲሁም በአፍሪካ መዲና አዲስ አበባ መልካም ቆይታ ያሳለፉበት መሆኑን አስታዉቀዋል።
በመጨረሻም በመርኃ ግብሩ ላይ ለተሳተፉ አካላት የምስጋናና የዕዉቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቷል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute