በምስለ ምርት (MVP) ደረጃ ላይ ለሚገኙ የኤ.አይ ስታርታፖች ሲሰጥ የነበረዉ የቡት ካምፕ ስልጠና ተጠናቀቀ።
· Education
The AI UniPod, jointly established by the Ethiopian Artificial Intelligence Institute, Addis Ababa University and UNDP, concluded a two-week bootcamp designed to strengthen MVP-stage AI startups through technical training, mentorship and innovation support.
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ዩኤንዲፒ በጋራ ባቋቋሙት የኤ.አይ ዩኒፖድ በምስለ ምርት ደረጃ ላይ የሚገኙና በኤ.አይ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ስታርታፖችን አቅም ለማጠናከር ያዘጋጀውን የ2 ሳምንት የቡትካምፕ ስልጠና ያጠናቀቁ ስታርታፖች የምርቃት መርሃ ግብር ተካሂዷል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ(ዶ/ር) ስታርታፖቹ ያላቸዉ የፈጠራ ሀሳቦች አስደናቂ መሆናቸዉን በመግለጽ ፤ተግባራዊ መሆን አለባቸው ብለዋል። ለዚህም ኢንስቲትዩቱ አስፈላጊዉን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
የዩ.ኤን.ዲ.ፒ ኢትዮጵያ ተወካይ ሳሙኤል ዶ (ዶ/ር) በበኩላቸዉ ዛሬየሚመረቁት ስታርታፖች ኤ.አይን በመጠቀም የማህበረሰቡን ችግር መፍታት እንደሚችል ማሳያ ናቸው ብለዋል፡፡ የፈጠራ ሃሳቦቹ ኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ተከታይ ሳይሆን ፈጣሪ ስለመሆኗም ያመላከተ ነው ብለዋል፡፡ ይህም ለሀገር እድገት ሚና አለዉ ሲሉ ገልጸዋል። የ ዩ.ኤን.ዲ.ፒ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል፡፡
የስልጠናዉ ተሳታፊዎች እና የዕለቱ ተመራቂዎች በቆይታቸዉ በቴክኖሎጂዉ የዉድድር ሜዳ ላይ ዉጤታማ የሚያደርጋቸዉን የቴክኒክ ክህሎት እና ልምድ ማግኘታቸዉን ገልጸዋል። ምርትና አገልግሎቶቻቸዉንም ለዕይታ አቅርበዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የሶስቱም ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት ለስታርታፖች፣አሰልጣኞች እንዲሁም አስተባባሪዎች የዕዉቅና ምስክር ወረቀት ሽልማት ተበርክቷል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute