“የሀገርን ችግር የመፍታት አቅም ያላቸዉ ስታርታፖችን ተመልክቻለሁ” የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)
· Visiting
EIH and EAII Strengthen Partnership to Empower Ethiopia’s Tech Startup Ecosystem
ዋና ስራ አስፈጻሚዉ ይህንን ያሉት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን በጎበኙበት ወቅት ነዉ። ኢንስቲትዩቱ ባስገነባዉ የኤ.አይ ስታርታፕ ማዕከል ባደረጉት ምልከታ የሀገርን ችግር የመፍታት አቅም ያላቸዉ ስታርታፖች መመልከታቸዉን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ስታርታፖቹ የሚያስፈልጋቸዉን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል። ኢንስቲትዩቱ የነገዋን ኢትዮጵያ መገንባት የሚችል አቅም ያላቸዉን ስራ ፈጣሪዎች ለማገዝ እያደረገ ያለው ተግባር የሚበረታታ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) የተመራዉ የተቋሙ ልዑክ አዲሱን የኢንስቲትዩቱን ዋና መሥሪያ ቤት ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute