በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር ሳዓድ ሙባረክ አል-ናኢሚ የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኘ፡፡
· MOU
Ambassador Saad Mubarak Al Naimi led a delegation to EAII, where discussions focused on the Institute’s mandate, strategic priorities, and opportunities to strengthen Ethiopia–Qatar cooperation in artificial intelligence and technological innovation.
በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር ሳዓድ ሙባረክ አል-ናኢሚ የተመራ ልዑክ ኢንስቲትዩቱን ጎብኝቷል፡፡
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ለልዑካን ቡድኑ ስለ ኢንስቲትዩቱ የስራ እንቅስቃሴ ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ኢትዮጵያ ከቴክኖሎጂው የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ ቁልፍ በሚባሉ ዘርፎች ላይ እየሰራቸው ስለሚገኙ ስራዎች በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል፡፡
በአምባሳደር ሳዓድ ሙባረክ አል-ናኢሚ የተመራው ልዑክ በኢንስቲትዩቱ የሚገኙትን የሮቦቲክስ ወርክሾፕ፣ የስታርታፕ ማዕከል፣ የዲጂታል ቤተ መጽሐፍት እና የምርት ማሳያ ክፍልን በጉብኝታቸው ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
ኢትዮጵያ እና ኳታር በቴክኖሎጂው መስክ ያላቸዉን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችላቸዉን ዉይይት በቀጣይ እንደሚያደርጉ በጉብኝቱ ወቅት ተመላክቷል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute