ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተዉጣጡ ልዑካን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ።
· Visiting
Foreign Affairs Delegation Reviews EAII’s Advancements Toward Becoming Africa’s AI Center of Excellence
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሀኑ ጸጋዬ የተመራ ልዑክ በኢንስቲትዩቱ የስራ ጉብኝት አድርጓል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ አዲሱን ዋና መስሪያ ቤት እና የተቋሙን የስራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ገለጻ አቅርበዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት የአፍሪካ የኤ.አይ የልህቀት ማዕከል ዋና መቀመጫ ኢትዮጵያ እንድትሆን እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጸዋል።
የዛሬዉ ጉብኝት እንደ ሀገር በዘርፉ ያለዉን አቅም ለማየት አጋዥ መሆኑንም አንስተዋል። ቀደም ሲል ኢንስቲትዩቱ አበልጽጎ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሰጠው በኤ.አይ የታገዘ ስርዓት ስራዎችን ያቀለለ መሆኑን በማንሳት ምስጋናቸዉን አቅርበዋል። ሚኒስትር ዴኤታዉ አክለዉም በሁለቱ ተቋማት መካከል የልምድ ልዉዉጥ ለማድረግ መልካም አጋጣሚ መሆኑን ተናግረዋል።
ልዑካኑ የሮቦቲክስ ወርክሾፕ፣ ዲጂታል ቤተ መጻሕፍት፣ የስታርታፕ ማዕከል እንዲሁም የምርት ማሳያ ክፍልን በጉብኝታቸዉ ተመልክተዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute