አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የቀዶ ጥገና ሐኪሞችን የአንጎል ዕጢ የማስወገድ ቀዶ ጥገናን በሂደት ላይ ባለበት ቅጽበት ለመጀመሪያ ጊዜ በመምራት በሕክምና ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ አስመዘገበ
· AI Solutions
Surgeons at London’s National Hospital for Neurology and Neurosurgery used real-time artificial intelligence during brain tumour surgery for the first time, helping safely remove Rhys Hibbert’s pituitary tumour while protecting his vision.
የዓለም የመጀመሪያው በቀጥታ በአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ (ኤአይ) የታገዘ የአእምሮ ቀዶ ጥገና የ48 ዓመቱን ራይስ ሂበርት እጢ በተሳካ ሁኔታ አስወግዶ እይታውን ከማጣት አድኖታል። በለንደን ብሔራዊ የነርቭ ሕክምና እና የነርቭ ቀዶ ጥገና ሆስፒታል በግንቦት ወር በተካሄደው ቀዶ ጥገና ወቅት ሐኪሞቹ ሙሉ ቁጥጥር ሲያደርጉ፣ በዩኬ የበለጸገው ኤአይ የቀጥታ የቀዶ ጥገናውን ቪዲዮ በቅጽበት በመተንተን ከ11 ሚሊ ሜትር የፒቱተሪ እጢ አጠገብ ያሉትን ወሳኝ ነርቮች እና የደም ቧንቧዎች በቀለም ኮድ ለይቶ በማመላከት ትክክለኛ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ዕጢን የማስወገድን ሂደት መርቷል። በዩሲኤል ሃውክስ ኢንስቲትዩት ቀደም ሲል በተሰበሰቡ በመቶዎች በሚቆጠሩ የፒቱተሪ ቀዶ ጥገና ቪዲዮዎች ላይ የሰለጠነው ይህ የኤ አይ "የቀዶ ጥገና ጉግል ካርታ" (surgical Google Maps) በሚመሳሰል መልኩ ተግባሩን ፈጽሟል። በጠባብና ጥቅጥቅ ባለው የአእምሮ ክፍል ውስጥ የሚሊሜትር ስህተት ወደ ዓይነ ስውርነት ሊያመራ ስለሚችል ኤአይ ይህንን አደጋ ለማስቀረት እጅግ ጠቃሚ ሆኖ ተገኝቷል። ከቤድፎርድሻየር የመጣው የሁለት ልጆች አባት የሆነው ሂበርት በፍጥነት አገግሞ ግልጽ የአይን ብርሃን
እይታውን አግኝቷል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute