በኢንስቲትዩቱ እየተገነባ ያለው አቅም ለቀጠናው ሀገራት ተደራሽ ሊሆን እንደሚገባ የአፍሪካ ህብረት ሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት ሚኒስትሮች ገለፁ።
· Visiting
AU Peace and Security Council Calls for Sharing Ethiopia’s AI Capacity to Advance Regional Growth, Peace, and Productivity.
የአፍሪካ ህብረት ሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት እና በአዲስ አበባ መቀመጫቸውን ያደረጉ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች የልምድ ልውውጥ ለማድረግ
ያለመ ጉብኝት በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አድርገዋል።
ለልዑካን ቡድኑ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) የተቋሙን የስራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ባደረጉት ገለፃ ኢንስቲትዩቱ እ.ኤ.አ በ2030
በአፍሪካ በዘርፉ ቀዳሚ ለመሆን ያስቀመጠውን ራዕይ ሊያሳኩ የሚችሉ ስራዎች በስፋት እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል።
በአፍሪካ ህብረት እና በተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ አምባሳደር ሒሩት ዘመነ በበኩላቸው በኢንስቲትዩቱ ያዩት የለውጥ ጉዞ እንዳስደነቃቸው ጠቅሰው የልዑካን ቡድኑ ጉብኝት ኢትዮጵያ በኤ.አይ ቴክኖሎጂ የደረሰችበትን ደረጃ ለቀጠናው ሀገራት ከማሳወቅ ባለፈ ተሞክሮዋን ለሌሎች ሀገራት ለማካፈል ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አምባሳደሮቹ ጉብኝቱን በማስመልከት በሰጡት አስተያየት፥ በኢንስቲትዩቱ የተመለከቱት የቴክኖሎጂ አቅም ለአህጉሪቷ ኩራት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ይህ የኤ.አይ ቴክኖሎጂ አቅም ወደ ሌሎች የቀጠናው ሀገራት ሊስፋፋ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ ጉብኝትአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን በአህጉሪቱ ሰላምና ፀጥታን ለማስፈለን ያለውን ሚና እና ከኢንስቲትዩቱ ጋር ተባብሮ መስራት የሚያስችሉ ጉዳዮችን ለመለየት ያለመ ነው።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute