ከኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ በመስራት የሀገሪቱን የህክምና ስርዓት በዲጂታል ቴክኖሎጂ ማሻሻል እንደሚቻል በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ሰራተኞች ተናገሩ፡፡
· Visiting
St. Paul’s Medical College and EAII Advance AI Collaboration to Transform Healthcare Innovation and Service Delivery
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ሰራተኞች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ሲጎበኙ የተመለከቱት የቴክኖሎጂ ውጤቶች እጅግ እንዳስደመሟቸው ገልጸዋል፡፡ከኢንስቲትዩቱ ጋር በመተባበር የሀገሪቱን የጤና አገልግሎት በዘመናዊ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ለማዘመን ያላቸውን ፍላጎትና እምነት ገልጸዋል።
የጤና ባለሙያዎቹ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በህክምናው ዘርፍ ማቀናጀት የህክምና ሂደቱን ፈጣን፣ ትክክለኛ እና ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል። ባለሙያዎችን የሚያግዙ ሲስተሞችን በመጠቀም ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት መስጠት እንደሚቻል አስገንዝበዋል። በተጨማሪም በኢንስቲትዩቱ የሚገኙትን የ3ዲ ፕሪንተሮች በመጠቀም በኮሌጁ ለሚማሩ የህክምና ተማሪዎች የተሻለና ተግባር ተኮር ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል አቅም መኖሩን አንስተዋል።
የኢንስቲትዩቱ አመራሮች በበኩላቸው በተለያዩ ዘርፎች እየተከናወኑ ስላሉ ስራዎች ገለጻ አድርገዋል። በተለይም ኢንስቲትዩቱ የጡት ካንሰርን፣ የህፃናት የቆዳ በሽታን፣ የስኳር በሽታን እና ሌሎች ተያያዥ ህመሞችን በመለየትና ለማከም የሚረዱ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ይህ የሁለቱ ተቋማት የጋራ ትብብር በኢትዮጵያ የህክምና ስርዓት ውስጥ የዲጂታል ለውጥን ለማምጣት ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል።
ሁለቱ ተቋማት ከዚህ ቀደም በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute