ኤ.አይ እና ሮቦቶች በፋርማሲዎች ላይ ያለውን ጫና እያቀለሉ ነው፡፡
· AI Solutions
UK pharmacy adopts AI-powered robot to automate prescription dispensing and ease staff workload.
በእንግሊዝ ውስጥ የሚገኝ ክሮስ ኬሚስት የተባለ ፋርማሲ በወር 11,000 ማዘዣዎችን ተቀብሎ መድኃኒት ለማሰራጨት ሮቦት እና የኤ.አይ ሶፍትዌሮችን ጥቅም ላይ እያዋለ ነው፡፡ ይህም በሰራተኞች እና በአገልግሎቶች ላይ ያለውን ጫና እያቀለለ ይገኛል ሲል ቢ.ቢ.ሲ ዘግቧል።
በሮቦቶቹ ላይ የተጫነው የኤ.አይ ሥርዓት የመጠቀሚያ ጊዜያቸው አጭር የሆኑትን መድኃኒቶች ቅድሚያ በመስጠትና መርጦ በማረጋገጥ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደርጋል።
ይህ የአውቶሜሽን ሂደት ፋርማሲስቶች ታካሚዎችን ለማማከር ጊዜ እንዲያገኙ እና የሙያ ክህሎታቸውን በተሻለ ሁኔታ ለመጠቀም እንደሚያስችላቸው ተመላክቷል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute