የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ አመራሮች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ፡፡
· Visiting
Ethiopian IT Park and EAII Strengthen Partnership to Advance AI Innovation, Digital Transformation, and Technology Ecosystems
የኢንስቲትዩቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ዘዉዴ ስለ ኢንስቲትዩቱ የምርምር ተግባራት፣በቴክኖሎጂው ዘርፍ ስለተሰሩ ፕሮጀክቶች እና ኢንስቲትዩቱ ዲጂታላይዜሽንን ለመደገፍ ስላለው ሚና ለጎብኚዎቹአብራርተዋል።
የኢትዮጵያ አይ.ቲ ፓርክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ በለጠ እሱባለው ጉብኝቱን አስመልክቶ በሰጡት ሀሳብ ኢንስቲትዩቱ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆንም ከእድሜው በላይ ብዙ እንደተጓዘ ገልፀዋል፡፡በኢንስቲትዩቱ ፓርኩን ከሰው ኃይል ጀምሮ እስከ ቁሳቁስ ድጋፍ ድረስ የተሻለ ቦታ ለማድረስ በቴክኖሎጂ የተደራጀ አቅም መኖሩን መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡ በዚህም በቅርበት መስራት ያለውን አስፈላጊነት አስረድተዋል፡፡
በኤ.አይ ምርምር፣ በተፈጥሮ ቋንቋ ቅንብር እና በሮቦቲክስ መስክ የተከናወኑ ተግባራትን፣ በዘመናዊ የኤ.አይ ቴክኖሎጂዎች የተደራጀዉን ሾዉ ሩም እንዲሁም የኢመርሲቭ ቴክኖሎጂን ኃላፊዎቹ ጎብኝተዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute