የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በልደታ ካቶሊክ ካቴድራል ት/ቤት የኤ.አይ ክበብ አቋቋመ።
· Education
EAII Supports Launch of New School AI Club to Inspire the Next Generation of Innovators
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ይታገሱ ደሳለኝ በክበቡ ምስረታ ላይ ለተማሪዎቹ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል። ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በንግግራቸዉ እንደገለጹት የኤ.አይ ቴክኖሎጂን አቅም ተገንዝባችሁ የሄዳችሁበት ርቀት የሚያስመሰግን ነዉ ብለዋል። ለክበቡ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ለማሟላትም ቃል ገብተዋል።
የልደታ ካቶሊክ ካቴድራል ት/ቤት ርዕሰ መምህር በላይ አባተ በበኩላቸዉ ት/ቤቱ በቴክኖሎጂ የታገዘ የማስተማር ዘዴ እንደሚከተል ገልጸዋል። የክበቡ መመስረት ይህንኑ ተግባር የሚያጠናክር እንደሚሆን ተስፋ እንዳላቸዉ አመላክተዋል። ከሀሳብ ጀምሮ እስከ ምስረታ ድረስ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።
ከምስረታዉ ጎን ለጎን የክበቡ አባላት የኢንስቲትዩቱን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል። ኢንስቲትዩቱ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የኤ.አይ ክበባትን ማቋቋሙ የሚታወስ ነዉ።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute